የመጽሐፉ ዓላማ
ይህ የግል ጥናት እና የጋራ መወያያ መጽሐፍ ተተኪውን ትውልድ በዋናነት ለመድረስ ታስቦ የተዘጋጀ ነው፡፡ ወጣቶች በፍጹም ቁርጠኝነት ጊዜአቸውን አመቻችተው በግላቸው እና በጋራ ሆነው በመወያየት እነዚህን ሁለት ወጣት ተኮር ወሳኝ መልዕክቶች ማለትም ማደግህ በነገር ሁሉ እንዲገለጥ ይህን አስብ የሚል ርዕስ የያዘውን ጳውሎስ ለወጣቱ አገልጋይ ለጢሞቴዎስ የጻፈውን መልዕክትና ብላቴና ነኝ አትበል ቀጥሎ ኤርምያስ ሆይ ምን ታያለህ የሚል ርዕስ የያዘውን እግዚአብሔር ለብላቴናው ኤርምያስ የተናገረውን፡- እነዚህን ሁለቱን ወጣት ተኮር ወሳኝ ምክሮችን ወጣቶች በግልና በጋራ እንዲያጠኑ ነው፡፡ እነዚህን መልዕክቶችን በትኩረት በመመልካትና በማጥናት የዛሬ ዘመናቸውንና ፍጻሜያቸውን ትልቅና የከበረ የሚያደርግ መንገድ እንዲመርጡና እንዲከተሉ ቀናውን ጎዳና ለማመልከት ታስቦ የተዘጋጀ ነው፡፡ እንዲሁም በታናሽነታቸው ወይም በወጣትነታቸው የላቀ አመለካከት፤ አስተሳሰብና ሁለንተናዊ ባላደራነትን አንግበው በማደግ ለብዙ ኃላፊነት እንዲዘጋጁ ለማበረታታት እና ለማነቃቃት የተዘጋጀ ነው፡፡